የነቀርሳ ማጣሪያ ምርመራዎችን በማካሄድ ጤንነትዎን መጠበቅ

የነቀርሳ ማጣሪያ ምርመራዎችን በማካሄድ ጤንነትዎን መጠበቅ ህይወትዎን ሊያተርፉት ይችላሉ።

እድሜዎት በ 50 እና 74 ዓመት መካከል ከሆነ :

  • ወንዶችና ሴቶች : የምርመራ ማድረጊያ እቃዎች ለርስዎ ይላክልዎትና በነጻ የሆድ እቃ ማጣሪያ ምርመራ ያደርጋሉ። ይህን ለማድረግ ቀላል እና ንጽህናው የተጠበቀና ፈጣን ይሆናል።

  • ሴቶች : በነጻ የጡት ማጣሪያ ቀጠሮ ለማቀናጀት በስልክ 13 14 50 መደወልና ለ BreastScreen Victoria ( ቪክቶሪያ ጡት ማጣሪያ መርመራ ) መጠየቅ።

ሴት ከሆኑና እድሚዎት በ 25 እና 74 መካከል ከሆነ : ለማህጸን ጫፍ ማጣሪያ ምርመራ ለማካሄድ ከሀኪምዎ  ወይም ነርስዎ ጋር ቀጠሮ ማቀናጀት።

እባክዎ እነዚህን ምርመራዎች ለርስዎና እና ለቤተሰብዎ በማካሄድ ጤንነትዎና ደህንነትዎ የተተጠበቀ ማድረግ።  

በራስዎ ቋንቋ የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ 13 14 50 መደወልማ እና ለ Cancer Council Victoria’ ( ቪክቶሪያ ነቀርሳ ምክር ቤት ) መጠየቅ።  

 

English equivalent